loading
ከአዲስ አበባ የተለያዩ የጤና ተቋማት የተውጣጡ የጤና ባለሙያዎች በጅግጅጋ ጉዳት ለደረሰባቸው 128 ሰዎች የህክምና አገልግሎት ሰጡ፡፡

የህክምና ቡድን መሪ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ትላንት አመሻሽ ላይ ከጅግጂጋ ሲመለሱ በቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ላይ ተገኝተው እንደገለጹት ቡድኑ በስምንት ቀን ቆይታው ለ128 ጉዳት ለደረሰባቸው ግለሰቦች የህክምና አገልግሎት ድጋፍ መስጠቱን ተናግረዋል፡፡
ከተጎጅዎቹ መካከልም ግማሽ ያህሎቹ የጭንቅላት፣ የደረት፣ የሆድና የደረት ቀዶ ጥገና ህክምና የተደረገላቸው መሆኑን ዶ/ር ብርሃኑ ገልጸዋል፡፡
የህክምና ቡድኑ ወደ ጅግጂጋ ከማቅናቱ በፊትም በድሬዳዋ ከተማ በተፈጠረው ግርግር ጉዳት ለደረሰባቸው ተጎጅዎችም የህክምና ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በድረ ገጹ እንዳስታወቀዉ 10 የቀዶ ጥገና ሃኪሞች፣ 3 አንስቴዮሎጂስቶች፣ 6 አንስቴቲስቶች እና 4 የኦፕሬሽን ክፍል ነርሶች በአጠቃላይ 23 የጤና ባለሙያዎች በህክምና ድጋፉ ተሳትፈዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *