loading
ከ37.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ ማዕድናት ባለፉት ዘጠኝ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡

ከ37.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ ማዕድናት ባለፉት ዘጠኝ መያዙን

የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡
ሚኒስቴሩ በተያዘዉ በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ በድምሩ 37 ሚሊዮን 488 ሺህ ,463.1 ብር የሚገመት ማዕድናት በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡
በገቢ ኮንትሮባንድ 19 ሚለዮን ,445 ሺህ ,983.10 ብር እና በወጪ ኮንትሮባንድ 18 ሚሊዮን ,42 ሺህ ,480 ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ማዕድናት በተለያዩ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች መያዝ ችሏል፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት ማዕድናት መካከል 19 ሚሊዮን 166 ሺህ 863.1 ብር የሚገመተው ብር፣ 11 ሚሊዮን 321 ሺህ ,600 ብር የሚገመተው ሌሎች ማዕድናት እና 7 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያለው ወርቅ ናቸው፡፡
ሀገራችን ከወርቅ የወጪ ንግድ የምታገኘው ገቢ በኮንትሮባድ እና ሌሎች ችግሮች ምክንያት መቀነሱን ሰሞኑን የተገለጸ ሲሆን ፤ ከአምስት ዓመታት በፊት ከ400 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ከወርቅ ስታገኝ የነበረ ቢሆንም ባለፈው ዓመት ከወርቅ የወጪ ንግድ የተገኘው ገቢ 30 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ብቻ ሆንዋል ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *