loading
ካሜሮን የሰዎችን የመዘዋወር መብት አልተጋፋሁም አለች

አርትስ 10/1/2011
የሜካሮን ባለስልጣናት ሰዎች ከደቡብ ምእራብ የሀገሪቱ ክፍል ወደ ሌላ አካባቢ እንዳይነቀሳቀሱ እገዳ ተጥሎባቸዋል የሚል ወሬ መሰራጨቱን ተከትሎ ነው ማስተባበያን የሰጡት፡፡
አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ጊልበርት ንጎንጎ በተባሉ የአካባቢው የትራንስፖርት ባለስልጣን ተፈረመ የተባለ ክልከላውን የሚገልጽ ደብዳቤ በማህበራዊ ድረ ገጽ ተሰራጭቷል፡፡
የደብዳቤው ይዘትም ማንኛውም ግለሰብ ህጋዊ ምክንያት ሳይኖረው እንግሊዘኛ ተናጋሪዎች የሚበዙበትን የደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱን ክፍል ለቆ መንቀሳቀስ አይፈቀድም የሚል ነው፡፡
የካሜሮን መንግስት ግን ይህ ፍጹም መሰረተ ቢስ ወሬ ነው በማለት የማስተባበያ ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ሰዎች ከዚህ አካባቢ የሚሰደዱት በቦታው ከመገንጠል ጥያቄ ጋር የተያያዘ ግጭት በመበራከቱ ነው ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *