loading
ኬንያ በሃገር ውስጥ ለሚመረቱ ሞባይል ስልኮች በጀት መደበች

አርትስ 15/02/2011

ኬንያ በሃገር ውስጥ ለሚመረቱ ሞባይል ስልኮችና የኮምፒውተር ግብዓቶች  ማምረቻ ድጋፍ የሚሆን 10 ሚሊዮን ዶላር መደበች፡፡

የኬንያ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሸን ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ጆ ሙቸሩ በኬናይሮቢ እየተካሄደ ባለው ዓመታዊ የአይሲቲ ጉባዔ ላይ እንደተናገሩት ኬኒያ በየሁለት ዓመቱ 50 ሚሊዮን የሚጠጉ የሞባይል ስልኮችን ከውጭ ሃገራት በግዢ ታስገባለች።

ይህ መሆኑ ደግሞ የሀገር ውስጥ ምርት ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ ሲያሳድር ተመልክተናል ይላሉ ሚኒስትሩ፡፡ ስለሆነም ይህ ችግር እንዳይቀጥል የሃገር ውስጥ አምራቾችን ማበረታታትና አቅማቸው እንዲጎለብት መስራት አለብን ብለዋል፡፡

አይ.ሲ.ቲ በኬንያ በፍጥነት እያደጉ ካሉ የኢንደስትሪ ዘርፎች  አንዱና ዋነኛው ሲሆን ለዚህም የተጠቃሚዎች ፍላጎት መጨመር እንደ ምክንያት ይጠቀሳል፡፡

በኬንያ 45 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሞባይል ተጠቃሚዎች እንዳሉ የቅርብ ጊዜ ጥናቶች ያመለክታሉ፤ ሮይተርስ እንደዘገበው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *