loading
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ለማስጀመር መዘጋጀቱን ገለፀ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2013 ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ለማስጀመር መዘጋጀቱን ገለፀ:: ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ታሳቢ ባደረግ መልኩ ትምህርት ለማስጀመር የሚያስችለውን ዝግጅት ማድረጉ ገልጿል። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሉኡካን በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ቅበላን በማስመልከት የመስክ ምልከታ አካሂዷል። በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል ዶክተር ኤባ ሜጀና በወቅቱ
እንደተናገሩት  ፤ዩኒቨርሲቲው ወረርሽኙን ለመከላከል ያከናወነው ተግባር የሚበረታታ ነው።

የተማሪዎች ማደሪያ፣ መማሪያና መመገቢያ አዳራሽና ሌሎች አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን ተዘዋውረው መመልከታቸውን ጠቅሰው፤ በዩኒቨርሲቲው ያለው ዝግጅት ተማሪዎችን ተቀብሎ ትምህርት ለማስጀመር የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው በሚመጡበት ወቅት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲሁም ሳኒታይዘር ለማቅረብ የተደረገው ዝግጅትም ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ሀብታሙ አበበ በበኩላቸው ተቋሙ  በጤና ሚኒስተር በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቃቸውን አስረድተዋል።በዚህም ለመጀመሪያ ዙር ከሶስት ሺህ ስድስት መቶ በላይ ተመራቂ ተማሪዎችን በመቀበል ትምህርታቸውን በአርባ አምስት ቀናት ውስጥ አጠናቀው ለምረቃ እንዲበቁ የማድረግ ስራ ይሰራል ብለዋል። ተማሪዎች ለወረርሽኙ ተጋላጭ እንዳይሆኑ በመመገቢያ አዳራሾች፣ መማሪያና ማደሪያ ክፍሎች እንዲሁም በቤተ መጽሀፍት አገልግሎት በሚያገኙበት ወቅት ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲገለገሉ
የሚደረግ መሆኑንም ተናግረዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *