ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ (ሲ.ፒ.ጄ) ኢትዮጵያ ውስጥ ከ14 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የታሰረ ጋዜጠኛ የለም አለ
ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ (ሲ.ፒ.ጄ) ኢትዮጵያ ውስጥ ከ14 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የታሰረ ጋዜጠኛ የለም አለ።
ኮሚቴው የፈረንጆቹን 2018 መጠናቀቅ አሰመልክቶ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ታግደው የነበሩ ከ260 በላይ ድረ-ገፆችን ክፍት ማድረጉን ገልጿል።
እንዲሁም ታስረው የነበሩ ጋዜጠኞች ሙሉ በሙሉ የተፈቱ መሆኑን ጠቅሶ እ.ኤ.አ. ከ2004 ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ምንም ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ያልታሰረባት አገር ሆናለች ሲል አስነብቧል።
ከውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያስረዳው መቀመጫውን በኒውዮርክ ያደረገው ኮሚቴው፣ ከዚህ ቀደም በጋዜጠኞች አያያዝ ዙሪያ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ተደጋጋሚ ክስ ያቀርብ እንደነበር ይታወሳል።