loading
ዘላቂ የኑሮ ማሻሻያ መርሃ ግብር በቀጣይ ዓመት ሊጀመር ነው

የከተሞች የምግብ ዋስትና አካል የሆነው ዘላቂ የኑሮ ማሻሻያ መርሃ ግብር በቀጣይ ዓመት ሊጀመር መሆኑን የፌዴራል የከተሞች የስራ እድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ አስታወቀ

ኤጀንሲው እንዳስታወቀው ወደ መርሀ ግብሩ የሚገቡት ሰዎች በምግብ ዋስትና ተጠቃሚ በመሆን ላይ የሚገኙ ናቸው።

የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰሎሞን አሰፋ እንዳሉት መርሀ ግብሩ ዘላቂ የኑሮ ማሻሻያ የሚል ስያሜ ያለው ሲሆን  በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙት የህብረተሰብ ክፍሎች ኑሯቸውን ከመደጎም አልፈው ራሳቸውን የሚችሉበት ነው ።

የዘላቂ የኑሮ ማሻሻያ መርሀግብሩን ወደ ስራ ለማስገባት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ነው አቶ ሰሎሞን የተናገሩት።

ለዚህም ከወዲሁ ተጠቃሚዎቹ ወደ ፊት ሊሰማሩባቸው የሚችሉባቸውን የስራ እቅዶች በማዘጋጀት ሊሰማሩበት ባቀዱት ስራ ላይም ስልጠናዎችን እየወሰዱ ነው ብለዋል።

እስካሁን 51 ሺ ሰዎች ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ የስራ እቅዳቸውን ማቅረባቸው የተገለጸ ሲሆን በቀጣይ ዓመት መርሀ ግብሩ ወደ ትግበራ እንደሚገባ  ኤጀንሲው አስታውቋል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል።

 

 

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *