loading
የሃበሻ አረቄና ጠጅን ጨምሮ ለስድስት ምርቶች ደረጃ ሊዘጋጅ ነው

አርትስ 12/02/2011

የኢትዮጵያ ደረጃዎች  ኤጀንሲ የጥናት እና ምርምር  ፈጠራ  ዳይሬክቶሬት  ዳይሬክተር  አቶ ሳሙኤል ደምሴ ለ አዲስ ዘመን  ጋዜጣ እንደገለፁት ኤጀንሲው በአሁን ወቅት  የጠጅ እና የሀበሻ አረቄን ጨምሮ  የቆሎ፣ የበሶ፤በርበሬ እና  ሽሮ ሀገረ በቀል ስድስት ምርቶችን  ደረጃ  እንዲያወጣ ሀሳብ የቀረበለት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ስድስቱ ምርቶች  በሌሎች ሀገራት  የሉም  ፤ ካሉም  በውጭ ሀገራት ያላቸውን  ደረጃ ወደኛ በማምጣት  መጠቀም የሚቻልበት  ሁኔታ  ይኖራል፤ ነገር ግን  ምርቶቹ በእኛ ሀገር  ብቻ የሚገኙ  በመሆናቸው  ደረጃ እንዲኖራቸው ለማድረግ  ጥናትና  እና ምርምር እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡

ለዚህም ታሰቦ የጥናት እና ምርምር  ዝግጅት  ወደ ተግባር  እንዲገባ ከዓለም  ባንክ  2. 5 ሚሊዮን  ብር   የተፈቅደ ሲሆን  ገንዘቡም እስኪለቀቅ እየተጠበቀ ነው በማለት ኃለፊው ተናግረዋል፡፡

እንጀራን ጨምሮ  ደረጃ እንዲዘጋጅላቸው  ሃሳብ ያቀረቡት   የተለያዩ ክፍሎች እና  የኢትዮጵያ  የምግብ  የመደሃኒትና የጤና  እንክብካቤ አስተዳደር  ቀጥጥር  ባለስልጣን  መሆናቸው ታውቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *