loading
የህብረተሰብን ጤና ለመጠበቅ ሁነኛ መፍትሄ ነው የተባለው የምግብና መድሃኒት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ለምክር ቤቱ ቀረበ።

የህብረተሰብን ጤና ለመጠበቅ ሁነኛ መፍትሄ ነው የተባለው የምግብና መድሃኒት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ለምክር ቤቱ ቀረበ።

አርትስ 03/04/11

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክር ቤቱ ላለፉት ስምንት ዓመታት ሲሰራበት የቆየውን የምግብና መድሃኒት አስተዳደር አዋጅ የሚተካውን ይህንን አዲስ ረቂቅ  በማየት ለሚመለከተው አካል መርቶታል።

ጤንነቱ ባልተጠበቀ ምግብና መድሃኒት ምክንያት የህብረተሰቡ ጤና አደጋ ላይ እንዳይወቅድ መከላከል የአዲሱ አዋጅ ቁልፍ ዓላማ ነው ብለዋል የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ጫላ ለሚ ።

አቶ ጫላ የረቂቁን ማብራሪያ ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት ይህ አዋጅ ደህንነቱና ውጤታማነቱ ባልተረጋገጠ የህክምና መሳሪያ ሳቢያ የሰው ህይወት ላይ የሚደርሰውን የጤና ችግር ለመከላከልና ለመቆጣጠር ይረዳል  ።

ነባሩን አዋጅ መቀየር ያስፈለገው የቁጥጥር ስራውን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስና በመስኩ ያለው የቴክሎጂ አጠቃቀም ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማሸጋገር ነው ተብሏል በማብራሪያው ። ዘገባው የኢዜአ ነው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *