loading
የሊቢያ መሪዎች በጣሊያን የሚያደርጉት ውይይት ሊቢያዊያንን ለሁለት ከፍሏል

አርትስ 03/ 03/2011

 

በሊቢያ ለሁለት ተከፍለው ሀገሪቱን እናስተዳድራለን የሚሉት ወገኖች በጣሊያን ፓርሌሞ ከተማ ድርድር ጀምረዋል፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ስብሰባው ምን ውጤት ያመጣል በሚለው ሀሳብ ሊቢያውያን የተከፋፈለ ስሜት ነው ያላቸው፡፡

በየትኛውም መንገድ ሰላም እንዲሰፍንላቸው የሚፈልጉት ነዋሪዎቹ አሁንም ተስፋ ሳይቆርጡ ከፓርሌመው ኮንፈረንሰ ብዙ ይጠብቃሉ፡፡

ሙዓመር ጋዳፊ በፈረንጆቹ 2011 ከስልጣናቸው በሀይል ከተወገዱ ጀምሮ በጀኔራል ካሊፋ ሀፍደታ እና ዓለም አቀፍ እውቅና ባለው በትሪፖሊ መንግስት ለሁለት ተከፍላ የምትተዳደረው ሊቢያ ሰላሟ ጥያቄ ውስጥ ከገባ ውሎ አድሯል፡፡

የአሁኑ የፓርሌሞ ኮንፈረንስ እንደተለመደው ከወሬ አያልፍም የሚሉ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ  ሁለቱ ተቀናቃኝ ወገኖች ከተግባቡ በቀጣዩ ጊዜ ሰላማዊ ምርጫ ተካሂዶ የተረጋጋ ህይወት መኖር እንጀምራለን የሚሉ ተስፈኞችም በርካቶች ናቸው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *