loading
የሎጂስቲክ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት ይደረጋል አሉ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ

አርትስ 27/02/2011

 

ሚኒስትሯ ይህንን ያሉት የሀገሪቱ ሎጅስቲክ ያለበትን ሁኔታ ለመመልከት የሞጆ ደረቅ ወደብን በጎበኙበት ወቅት ነው፡፡ የባህርትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ባለስልጣን ዋናስራ አስፈፃሚ  አቶ ሮባ መገርሳ እንዲሁምየሚመለከታቸው ኃላፊዎች ለሚኒስትሯ ገለፃ አድርገውላቸዋል፡፡

እንደ ትራንስፖርት ሚኒስቴር መረጃ  የሞጆ ደረቅ ወደብ ያሉበትን ችግሮቹን ለመፍታት ከአዳዲሶቹ አመራሮች ብዙ ስራ ይጠበቃል ፡፡

ሚኒስትሯ በዘርፉ የሚታዩትን ችግሮች በዘላቂነት ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል ብለዋል፡፡

በጉብኝቱ የተሳተፉት የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለሀገራዊ እድገት ግንባታ በየዘርፋችን መረባረብ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *