loading
የመርሲ ሳይድ ደርቢ ግጥሚያ ዛሬ ምሽት ይደረጋል

የመርሲ ሳይድ ደርቢ ግጥሚያ ዛሬ ምሽት ይደረጋል

 

የ29ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ትናንት መካሄድ ጀምረዋል፡፡
ትናንት በተጠበቀው የሰሜን ለንደን ደርቢ ጨዋታ ዊምብሌይ ላይ ቶተንሃም ከአርሰናል በአንድ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፤ አሮን ራምሴ መድፈኞቹን ቀዳሚ ሲያደርግ ሀሪ ኬን ለስፐርሶች በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል፡፡
ምሽት ላይ ደግሞ ማንችስተር ሲቲ ቦርንመዝን በሪያድ ማህሬዝ ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 ረትቷል፤ ማንችስተር ዩናይትድ ሳውዛምፕተንን ከመመራት ተነስቶ 3 ለ 2 ድል አድርጓል፡፡ ሮሜሉ ሉካኩ 2×፣ ፔሬራ ከመረብ ሲያገናኙ፤ ቫለሪ እና ዋርድ ፕራውስ ለደቡብ ጠረፉ ቡድን አስቆጥረዋል፡፡
በሌሎች ጨዋታዎች ብራይተን 1 ለ 0 ሀደርስፊልድ፣ በርንሊ 1 ለ 3 ክሪስታል ፓላስ፣ ወልቭስ 2 ለ 0 ካርዲፍ ሲቲ እንዲሁም ዌስት ሃም 2 ለ 0 ኒውካስትል ዩናይትድ ተለያይተዋል፡፡
ዛሬ ምሽት 1፡15 ተጠባቂው የመርሲ ሳይድ ደርቢ፤ ኢቨርተን በጉዲሰን ፓርክ ሊቨርፑልን ያስተናግዳል፡፡
በሌላ የደርቢ ስያሜ የሚጠራው የጓደኛሞች ደርቢ ፍልሚያ ለ233ኛ ጊዜ ሲከናወን እስካሁን በተደረጉ ፍልሚያዎች ቀያዮቹ በ93ቱ የበላይነት አላቸው፡፡አላቸው፡፡

በሌሎች ጨዋታዎች ዋትፎርድ ከሌስተር ሲቲ 9፡00 ሲጫወቱ፤ በምዕራብ ለንደን ደርቢ ፉልሃም በአዲሱ አሰልጣኝ ስኮት ፓርከር እየተመራ በክራቨን ኮቴጅ ቼልሲን 11:05 ላይ ይገጥማል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *