loading
የመንግስታቱ ድርጅት ማሳሰቢያ

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 29፣ 2012  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻይና በሆንግኮንግ ላይ ያወጣችውን የብሄራዊ ደህንነት ህግ አወገዘ::የድርጅቱ የሰብዓዊ መብቶች ኤክስፐርቶች ለቤጅንግ በፃፉት ባለ 14 ገፅ ደብዳቤ በሆንግኮንግ ላይ የተላለፈው እስረኞችን ለማእከላዊ ቻይና አሳልፎ የመስጠት ህግ ነፃነትን የሚጋፋ ነው ብለዋል፡፡

ቻይና ይህን ህግ ዳግም ካልፈተሸችው በስተቀረ አደጋ አለው ያሉት ባለ ሙያዎቹ ህጉ ከተላለፈ ጀምሮ የተቀሰቀሰው አመፅ አንዱ ማሳያ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው አመፁን ተከትሎ በተቃዋሚዎች እና በፖሊሶች መካከል በተፈጠረ ግጭት ሰዎች  ለሞት እና ለእስር ሲዳረጉ በርካታ ንብረት ወድሟል፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችም ድርጊቱን በጥብቅ አውግዘውታል፡፡

የደህንነትና የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ተነጣጥሎ አይታይም ያለው የድርጂቱ ደብዳቤ ቤጅንግ ይህን ታሳቢ በማድረግ የችግሩ ሳይሆን የመፍትሄው አካል መሆን አለባት ብሏል፡፡ ኤክስፐርቶቹ በሰጡት የህግ ትንተና ዓለም አቀፍ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን ከፀጥታ ጋር የተያያዙ ህጎች እና ሽብርተኝነት በትክክል መተርጎምና መብራራት አለባቸው ብለዋል፡፡ ይህን ያሉበት ዋነኛ ምክንያት ደግሞ ቻይና ሆንግኮንግ ውስጥ ለወራት የዘለቀውን ህዝባዊ አመፅ ከሽብርተኝነት ጋር ስታያይዘው በመታየቷ ነው፡፡ ቻይና ግን የሆንግኮንግ ችግር የሚፈታው በራሷ በቻይና እንጂ በማንም ወገን ጣልቃ ገብነት አይደለም የሚል ፅኑ አቋም ነው ያላት፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *