የመንግስት ንግድ ቤት ተከራዮች የቤቶች ኮርፖሬሽን የወሰነውን የዋጋ ጭማሪ በድጋሚ እንዲያጤንላቸው መንግስትን ጠየቁ
የመንግስት ንግድ ቤት ተከራዮች የቤቶች ኮርፖሬሽን የወሰነውን የዋጋ ጭማሪ በድጋሚ እንዲያጤንላቸው መንግስትን ጠየቁ፡፡
ነጋዴዎቹ ይህን የጠየቁት ዛሬ በግሎባል ሆቴል አዳራሽ ባደረጉት የጋራ ውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡
በውይይታቸውም ለቤት ኪራይ የተወሰነው ውሳኔ በበቂ ጥናት ላይ ያልተመሰረተ እና በቂ ባለሙያዎችን ያሳተፈ አይደለም ብለዋል፡፡
አቋማችን ጭማሪው አይደረግ የሚል ሳይሆን ተመጣጣኝ ጭማሪ ይደረግ የሚል ነው ብለዋል፡፡
ውሳኔው ነጋዴዎቹ ከቤታቸው የማፈናቀል እንደሚያስከትል፣ የድርጅቶቹን ሰራተኞች ህልውናም አደጋ ውስጥ ሊከት የሚችል ነው ብለዋል፡፡
በአጠቃላይ ከአዲስ አበባ ብቻ 6 ሺ 635 የመንግስት ቤት ተከራይ ነጋዴዎች ያሉ ሲሆን በስራቸውም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞችን ያስተዳድራሉ። መረጃው የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ነው።