የማሊ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት የኬታን አሸናፊነት ይፋ አድርጓል፡፡
በማሊ በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ኢብራሂም ቡበከር ኬታ ለሁለተኛ ጊዜ ማሸነፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወዳዳሪዎች የኬታን ማሸነፍ አንቀበልም በማለታቸው ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት አምርቶ ነበር፡፡
እጩ ተፎካካሪ ሆነው የቀረቡት ሱሜይላ ሲሴ ውጤቱ ይፋ በተደረገ ማግስት ይህ የማሊያዊያንን ደምጽ የሚወክል ውጤት አይደለም አንቀበለወም ነበር ያሉት፡፡
የኋላ ኋላ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እንዲታይ ተደርጎ ኬታ 67.2 በሆነ ድምጽ አሸናፊነታቸው ተውቋል፡፡
ተቀናቃኙ ሲሴ ግን የደጋፊዎቻችን ድምጽ ባይሰረቅ ኖሮ 51 በመቶ እንደምናሸንፍ እርግጠኞች ነበርን ብለዋል፡፡