loading
የራያ ህዝብ የማንነት ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኝ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ፓርቲ ጠየቀ

አርትስ 23/02/2011

 

የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ኢንጅነር ግደይ ዘርዓፅዮን ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት፤ በትግራይና በአማራ ክልል ውስጥ ያሉ አንዳንድ የፖለቲካ አመራሮችለግል ጥቅማቸው ሲሉ በሚነዙት የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ ምክንያት የራያ ህዝብ የማንነት ጥያቄ ምላሽ አጥቷል፡፡

በዚህም የህዝቡ ደህንነት አደጋ ላይ ወድቋል ብለዋል፡፡

በህዝቡ የተነሳውን ጥያቄ ሁለቱ ክልሎች ተመካክረው ሊፈቱት ይገባ የነበረ ቢሆንም ለጉዳዩ በቂ ትኩረት ባለመስጠታቸው ምክንያት አንዱ ክልል በሌላው ላይመንገድ እስከመዝጋት የሚደርስ ተግባር የሚፈፀምበት ሁኔታ መኖሩን ምክትልሊቀመንበሩ ተናግረዋል፡፡

«ፓርቲያችን በሁለቱም ክልሎች በየጎዳናው የሚደረገው ዛቻና ፉከራ ለማንም ይጠቅማል ብሎ አያምንም» ያሉት ምክትል ሊቀመንበሩ ፤የራያ ህዝብ ጥያቄበህገመንግስቱ መሰረት ወደ ፈዴሬሽን ምክር ቤት መጥቶ በህግ አግባብ ውሳኔ መሰጠት ይኖርበታል ብለዋል፡፡

«እኛ አሁን የምንጠይቀውና ጫና የምናደርገው የትግራይ ክልል መንግስትን ነው» ያሉት ምክትል ሊቀ መንበሩ ጉዳዩ በሌላ አካል ባይቀርብም እንኳ የክልሉመንግስት ራሱ ለፌዴራል መንግስት ጥያቄ በማቅረብ እልባት እንዲያገኝ ማድረግ የሚጠበቅበት መሆኑን ተናግረዋል፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *