loading
የሱዳን ተፎካካሪ ፓርቲዎች የአልበሽርን እጩነት ተቃወሙት፡፡

ሱዳን እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 በምታካሂደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፕሬዝዳንት ኡመር ሀሰን አልበሽር ለሶስተኛ ጊዜ እጩ ተወዳዳሪ ሆነው ይቀርባሉ፡፡
በሀገሪቱ ያሉት 28ቱም ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ ይህን ሀሳብ አይደግፉትም፡፡ አልበሽር ግን በ2005 የተሻሻለው የሀገሪቱ የሽግግር ህገ መንግስት በመጭው ምርጫ እንዲፎካከሩ ይፈቅድላቸዋል ተብሏል፡፡
ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው በሀገሪቱ ያሉት ፓርቲዎች አንድ የፖለቲካ ግምባር በመፍጠር ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው ለመቅረብ እየተዘጋጁ ነው፡፡
ፓርቲዎቹ የሪፎርም ናው ፓርቲ ጸሀፊ የሆኑትን ጋዚ ሳላህ አል ዲንን የጋራ እጩ አድርገው ለማቅረብ ዕቅድ እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡
ሀገሪቱን በመንግስትነት የሚመራው ብሄራዊ ኮንግረስ ፓርቲ ግን ፕሬዝዳንት አል በሽርን እጩ ተወዳዳሪ አድርጎ ለማቅረብ ወስኗል፡፡

አርትስ 24/12/2010

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *