loading
የስራ ስምሪት ባልተጀመረባቸው ሀገራት የሚደረግ ጉዞ ላይ እገዳ ተጣለ

የስራ ስምሪት ባልተጀመረባቸው ሀገራት የሚደረግ ጉዞ ላይ እገዳ ተጣለ

አርትስ 20/02/2011

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት የተለያዩ የቪዛ አይነቶችን በመጠቀም የስራ ስምሪት ወዳልተጀመረባቸው ሃገራት የሚደረግ ጉዞ መታገዱን ተናግረዋል።

እንደሚኒስትር ዲኤታው ገለጻ በአዲሱ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት መመሪያ መሠረት ዜጎች ለስራ መሰማራት የሚችሉት የሁለትዮሽ ስምምነት ወደ ተፈረመባቸው ሀገራት ብቻ ነው፡፡

የሁለትዮሽ ስምምነት ተደርጎ ሰራተኞችን ለመላክ ቅድመ ዝግጅት የተደረገባቸው ሀገራት ሳውዲ አረቢያ፣ ኳታር እና ጆርዳን መሆናቸውን የጠቆሙት ሚኒስቴር ዴኤታው መስፈርቱን የሚያሟሉ ዜጎችንለጉዞ የመመልመል ስራ እንጂ ጉዞ አለመጀመሩን ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ ባለፈ የሁለትዮሽ ስምምነት ካልተደረሰባቸው ሀገራት መካከል ወደ ኩዌት፣ ባህሪን፣ ቤይሩት እና ኦማን  በቱሪስት፣ በዘመድ ጥየቃ፣ በጉብኝት እና በነጋዴ ቪዛ በሚደረግ ጉዞ ዜጎች አደጋ ላይእየወደቁ በመሆኑ በዚህ መልክ ሲደረግ የነበረ ህገ ወጥ ዝውውር ላይ ክልከላ መደረጉን ሚኒስቴር ዴኤታው ገልፀዋል፡፡

የፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ክፍል ሀላፊ ኮማንደር ከተማ ደበላ በበኩላቸው ህገ ወጥ ዝውውርን የሚከላከል ግብረ ሀይል መቋቋሙን ጠቁመው በህገ ወጥ ዝውውር ላይ የተሰማሩ አካላት ላይእርምጃ መውሰድ እንደሚጀመር አሳስበዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *