የቀድሞው የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ናጅብ ራዛቅ በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ተባሉ::
አዲስ አበባ፣ሐምሌ21፣ 2012 የቀድሞው የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ናጅብ ራዛቅ በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ተባሉ:: እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2009 እስከ 2018 ማሌዢያን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት ናጅብ በሰባት ክሶች ነው ጥፋተኛ ሆነው የተገኙት፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው ናጅብ የቀረቡባቸውን ክሶች በሙሉ አልፈፀምኩም በማለት ቢቃወሙም አቃቤ ህግ ያቀረበባቸውን ክስ በማስረጃ በማረጋገጡ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ 10 ሚሊዮን ዶላር የመንግስት ገንዘብ በስማቸው በተከፈተ አካውንት እንዲዞር ማድረጋቸው በፍርድ ቤት የተረጋገጠባቸው ሲሆን በጠቅላላው የተከሰሱባቸው ወንጀሎች እንያንዳንዳቸው ከ15 እስከ 20 ዓመት ድረስ በእስር ሊያስቀጡ ይችላሉ ነው የተባለው፡፡ ናጅብ የአሁኑ ወሳኔ የተላለፈባቸው ከ2011 እስከ 17 ድረስ ለመንግስት ያልከፈሉት ታክስ ከነቅጣቱ ተሰልቶ 400 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍሉ ከተወሰነባቸው ከ6 ቀናት በኋላ ነው፡፡