የብድር እጦት የኬንያን ግብርና ማምረቻ ኢንደስትሪ እግር ከወርች አስሮታል
የኬኒያ ብሄራዊ ባንክ መረጃ እንደሚያመለክተዉ በሃገሪቱ 85 በመቶ ብድር ለግለሰቦች የሚሰጥ ሲሆን አንድ በመቶ የሚሆነዉ ብድር ብቻ ለግብርና ዘርፍ የሚዉል ሆኖ 0.16 በመቶ ብድር ደግሞ ለማምረቻዉ ዘርፍ ይመደባል፡፡
በኬኒያ የግብራናና የማምረቻ ዘርፉ በሚፈለገዉ ልክ የማይደገፍ በመሆኑም ሃገሪቱ ለከፋ የምግብና የሃገር ዉስጥ ምርት እጥረት እንዲጋረጥባት አድርጓታል፡፡
የሃገሪቱ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች የግብርና ዘርፍ ምልከታ በሚለዉ የጥናት ሪፖርት የግብርናዉ ዘርፍ በመደበኛዉ የባንክ ሴክተር እይታ አስጊ የሚባል ነዉ ሲል ኢስት አፍሪካን የሃገሪቱ የዜና ምንጭ ዘግቧል፡፡