![](http://43.156.135.34.bc.googleusercontent.com/wp-content/uploads/2018/11/TIBOR.png)
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ረዳት ተጠሪ ቲቦር ናግይ ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡
አርትስ 19/03/2011
ረዳት ተጠሪው በጉብኝታቸው ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ቆይታ እንደሚያደርጉ ተገልጿል፡፡ረዳትተጠሪው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ህዳር 29 በሚያደርጉት ቆይታ ጅቡቲ፣ ኤርትራ እና ኬንያን ይጎበኛሉ ተብሏል፡
በጉብኝታቸውም አሜሪካ ከአፍሪካ ጋር በንግድ ፣ በሰላም እና ደህንነት ዙሪያ በጋራ በምትሰራባቸው ጉዳዮች ዙሪያከሀገራቱ መሪዎች ጋር እንደሚመክሩም ነው የተገለጸው።
የአፍሪካ ህብረት በአዲስ አበባ በሚያካሂደው ከፍተኛ የምክክር መድረክ ላይም ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ዘገባው የፋና ነው