loading
የአሜሪካ ማዕከላዊ ባንክ የሥራ አጦች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ እንዳሳሰበው ገለፀ

ባለፈዉ ሳምንት ብቻአንድ ነጥብ አምስት አሜሪካዊያን የስራ አጥነት ፎርም መሙላታቸው ኮቪድ 19 በሀገሪቱ ጫናውን እንደቀጠለ መሆኑን ያመላክታል ተብሏል፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው በአሜሪካ ለ13 ተከታታይ ሳምንታት የሥራ አጦች ቁጥር ከ1 ሚሊዮን በላይ እየሆነ መመዝገቡ ተስተውሏል፡፡

ይህን ያስተዋለው የሀገሪቱ ማእከላዊ ባንክ አስቸኳይ የኢኮኖሚ ማስተካከያ ካልተደረገ ችግሩ ከዚህም የከፋ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡

ምንም እንኳ አሜሪካ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ተዘግተው የነበሩ የንግድ ተቋማትን መክፈት የጀመረች እና ሰዎች ወደ ስራ መመለስ ቢጀምሩም የስራ አጦች ቁጥር ግን በሚፈለገው መጠን መቀነስ አላሳየም ተብሏል፡፡

ይሁን እንጂ አዳዲስ የተከፈቱት የቢዝነስ ተቋማት 2 ነጥብ 5 ያህል የስራ እድል መፍጠራቸውን ተከትሎ የሥራ አጦችን መጠን ወደ 13 በመቶ ዝቅ እንዳደረገው ይነገራል፡፡

በቅርብ የወጣ ሪፖርት እነደሚያሳየው ከሆነ ከ29 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች የሥራ አጥነት ካርድ ይዘው ድጎማ በመቀበል ላይ ይገኛሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *