loading
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ቲበር ናዥ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በሰላም ሚኒስቴር ጀመሩ

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ቲበር ናዥ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በሰላም ሚኒስቴር ጀመሩ

አርትስ 23/03/2011

 ረዳት ሚኒስትሩ ከሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈርያት ጋር ከነበራቸው ውይይት በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ላሉ ለውጦች መንግሥታቸው ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡

የአሁኑን ሥልጣን ከያዙ ጀምሮ ለመጀመርያ ጊዜ ባደረጉት ጉብኝት በኢትዮጵያ እየታዩ ያሉ ለውጦች መልካም መሆናቸውንና አሜሪካ ኢትዮጵያን በቀጣናው ብቻ ሳይሆን በአኅጉሪቱም ዋነኛ አጋር አድርጋ እንደምትመለከታት አስረድተዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በቀጣይ በሠላም ግንባታ፣ የህግ የበላይነትን በማስፈን ፣ በሰው ኃይል ግንባታና በሌሎች ዘርፎች ላይ ለመስራት ተወያይተዋል፡

ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እና  ከመከላከያ ሚኒስትሯ ጋር ውይይት ያደረጉት ቲቦር ናዥ በቀጣይ ጎዟቸውን  ወደ ኤርትራ፣ ኬንያና ጂቡቲ አድርገዋል፡፡ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር የአፍሪካ ዕዝ ወደሚገኝበት ጀርመን ስቱትጋርትም ያቀናሉ ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *