loading
የአውሮፓ ፓርላማ ማዕቀብ እንዲጣል ጠየቀ::

አበባ፣ መስከረም 28፣ 2014 የአውሮፓ ፓርላማ አባላት በሠሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ በቀጣይ ሦስት ሳምንታት ውስጥ መሻሻል:: የማያሳይ ከሆነ በጦርነቱ ተሳታፊ በሆኑ አካላት ላይ ማዕቀቦች እንዲጣል ጠየቁ የአውሮፓ ፓርላማ ሐሙስ መስከረም 27/2014 ዓ.ም ያደረገውን ስብሰባ ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ላይ ለግጭቱ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲገኝ ጠይቋል።በዚህም መሠረት የፓርላማው አባላት በጦርነቱ አካባቢ ያለው የሰብዓዊ ሁኔታ እስከ ፈረንጆቹ ጥቅምት ወር መጨረሻ ማለትም ጥቅምት 21/2021 ዓ.ም ድረስ በከፍተኛ ሁኔታ መሻሻል የማያሳይ ከሆነ ኮሚሽኑ በጦርነቱ ተሳታፊዎች ላይ ማዕቀብ እንዲጥል ጠይቀዋል።

በዚህም መሠረት ፓርላማው ዕቀባው ያመለከታቸው ወገኖችን የጠቀሰ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የኤርትራ መንግሥት፣ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እንዲሁም ግጭቱ እንዲራዘም እና እንዲባባስ አስተዋጽኦ አላቸው ያላቸውን አካላት ጠቅሷል።የአውሮፓ ፓርላማ አባላት ትናንት ሐሙስ በሠሜን ኢትዮጵያ ግጭት እና የሰብዓዊ እርዳታ እቅርቦት እክሎች በአስቸኳይ እንዲወገዱ ባወጡት የውሳኔ ሃሳብ ላይ ጠይቀዋል።

በትግራይ ሕገመንግሥታዊ ሥርዓት መልሶ እንዲሰፍንና የተኩስ አቁም ተደርጎ አስፈላጊው ቁጥጥር ዘዴ እንዲቋቋም ጠይቀው፤ በሌሎችም የኢትዮጵያ አካባቢ ያለው የሰብአዊ ችግር ሁኔታ እያሽቆለቆለ መሆኑን አሳስቧል።ፓርላማው ባደረገው ስብሰባ ላይ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ 618 ድጋፍ፣ 4 ተቃውሞ እና 58 ድምጸ ታቅቦ ተቀባይነት አግኝተወል ሲል ከፓርላማው የወጣው መግለጫ አመልክተዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *