የአየርላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድከር በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸውን ጀመሩ
የአየርላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድከር በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸውን ጀመሩ
አየርላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊኦ ቫራድካርን በኢትዮጵያ የሶስት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ የገቡት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ግብዣ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ማርቆስ ተክሌ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድከር በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ጋር በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ነው የተነገረው።
በዚህ መሰረትም ሊዮ ቫራድከር በኢትዮጵያ በሚያደርጉት የሶስት ቀናት የስራ ጉብኝት ጅማሬያቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።
ኢትዮጵያ እና አየርላንድ ረዥም ዘመን ያስቆጠረ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፤ እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር በ2014 የአየርላንድ ፕሬዝዳንት ሚካኤል ሄገንስ ኢትዮጵያን ጎበኝተዋል።
በወቅቱም አየርላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የ136 ሚሊዮን ዩሮ የልማት ትብብር መፈራረሟ ይታወቃል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እና በቀጠናው አንፃራዊ ሰላም እንዲሰፍን ለምታደርገው እንቅስቃሴ አየርላንድ ድጋፍ ስትሰጥ ቆይታለች።
ኢትዮጵያና አየርላንድ ረጅም ዘመን ያስቆጠረ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፣ አየርላንድ ቆንስላዋን በ1986 ዓ.ም አዲስ አበባ ላይ ስትከፍት ኢትዮጵያ ደግሞ በ1995 ዓ.ም ደብሊን ላይ ኤምባሲዋን መክፈቷ ይታወሳል።