loading
የአዲስአበባ ከተማ የከንቲባ ፅ/ቤት ህግን ያልተከተለ ብልሹ አሰራር ሲገጥማችሁ በእነዚህ የስልክ መስመሮች ጠቁሙኝ ብሏል

የአዲስአበባ ከተማ የከንቲባ ፅ/ቤት ህግን ያልተከተለ ብልሹ አሰራር ሲገጥማችሁ በእነዚህ የስልክ መስመሮች ጠቁሙኝ ብሏል

አርትስ 07/ 04 /2011

 አዲስ የተቋቋመው የጥቆማ መስጫ ማእከል  ሙሉ በሙሉ በከንቲባ ፅ/ቤት ይመራል፤

ከህዝብ የሚሰበሰብ ቅሬታን እና ጥቆማን የሚያጣራ በከንቲባ ፅ/ቤት የሚመራ ግብረሃይል ተቋቁሟል፤ ከአጣሪ ግብረሃይሉ ጋር በመሆን በየዕለቱ ለከንቲባው ሪፖርት የሚያቀርብ ኮሚቴም ተቋቁሟል፤ ቅሬታ ተቀባዮቹ(ኦፕሬተሮች) ከማንኛውም አካል ነፃ እና ተጠሪነታቸውም ለከንቲባ ፅ/ቤት ብቻ የሆኑ ሲሆን ፤ ድርሻቸውም በስልክ ከህዝብ የቀረበን ጥቆማ እና አቤቱታ ለኦፕሬቲንግ ሲስተም አስተባባሪው ማድረስ ብቻ ይሆናል ብሏል ፅ/ቤቱ፡፡

የስልክ አጠቃቀሙን በተመለከተ ፤ ለእያንዳንዱ  ክ/ከተማ የሚቀርብ ቅሬታ እና ጥቆማ በተሰጠው የስልክ መስመር በመጠቀም ማድረስ ይቻላል፡፡ ነገር ግን  መጠቆም ያለበት በየወረዳው እና ክፍለከተማው ያለውን አመራር ብቻ ሳይሆን በህገ-ወጥ መንገድ የተያዘ የመኖሪያ ቤት ፥ የታጠረ መሬት ፥ የንግድ ሼድ እና ማንኛውንም ኢ-ፍትሃዊ ድርጊት ሲመለከት ለፅ/ቤቱ ጥቆማ በማድረግ የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ ሲል አሳስቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *