loading
የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ከያንያን በባህርዳር ጉብኝት ጀመሩ

አርትስ 15/03/2011

ትናንት ማምሻውን ባህርዳር የገቡት የአዲስ አባባ ወጣቶችና የኪነጥበብ ባለሞያዎች ዛሬ ጣና ቂርቆስን ለመጎብኘት እና እንቦጭን ለመከላከልወደ ቦታው አቅንተዋል፡፡
የጉዞው ዋና ዓላማዎችም በባሕር ዳር እና አዲስ አበባ ህዝቦች መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር፣በጣና ሀይቅ ላይ የተጋረጠውን የእንቦጭአረም በጋራ መከላከል እና በሁለቱ ከተሞች ያለውን ትብብር በማሳደግ በጋራ መስራት ነው፡፡
ዛሬ  ልዑኩ በባህርዳር ከተማ  የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን ይጎበኛል፤ነገ ደግሞ ወደ ጣና ገዳማት በመጓዝ በጣና ሀይቅ ላይ የተጋረጠውንእንቦጭ በመከላከል የድርሻውን እንደሚወጣ ታውቋል፡፡

አብመድ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *