loading
የአዲስ አበባ ገቢዎች ባለስልጣን ህግና ደንብ ጥሰዋል ያላቸዉን 18 ሰራተኞች ከስራ አሰናበተ

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፥ ደንበኞችን የማያከብሩ፣ መድሎ የሚፈጽሙና የስነ ምግባር ችግር የታየባቸው 18 ሰራተኞች ከስራ ተሰናብተዋል፣ 102 ሰራተኞች ማስጠንቀቂያ የደረሳቸዉ ሲሆን 15 ያህሉ ደግሞ ከደረጃና ደሞዝ ዝቅ እንዲሉ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።

ባለፈው ዓመት ከደንበኞች አገልፍግሎት ጋር በተያያዘ 320 ሺህ ያህል ቅሬታዎች መስሪያ ቤቱ ላይ መቅረባቸውን የተናገሩት ዳይሬክተሩ፥ ወደ ግብር ይግባኝ ሰሚ የተሸጋገሩት 3 ሺህ ያህል ናቸው ብለዋል።

ባለስልጣኑ በያዝነው በጀት ዓመት 44 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ከግብር እና ቀረጥ ለመሰብሰብ እቅድ እንዳለው ተናግረዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *