የአዴኃን አመራሮችና ወታደሮች ባሕር ዳር ገቡ
የአዴኃን አመራሮችና ወታደሮች ባሕር ዳር ገቡ፡፡
አርትስ 05/13/2010
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ(አዴኃን) የአዴኃን አመራሮች እና ወታደሮች ጎንደር ከተማ የተደረገላቸውን አቀባበል አጠናቀው ባሕር ዳር ገብተዋል፡፡
የአማራ መገኛኛ ብዙሃን ኤጀንስ እንዳስታወቀው አዴኃን መቀጫውን ኤርትራ በማድረግ የትጥቅ ትግል ሲያደርግ የነበረ ድርጅት ነው፡፡በቅርቡ መንግስት ያደረገውን ለውጥ ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ከመንግስት ጋር ስምምነት ላይ መድረሱ ይታወቃል፡፡
በአስመራ ከአማራ ክልል አመራሮች ጋር ባደረገው ድርድርም ትጥቁን ፈትቶ ወደ ሀገር ቤት ለመግባት ቃል ገብቶ ነበር፡፡ድርጅቱ በስምምነቱ መሰረትም አሁን ላይ አመራሮቹንና ወታደሮቹን ይዞ ባሕር ዳር ገብቷል፡፡
የአዴኃን አመራሮች እና ወታደሮች ከኤርትራ በረሃ ኦማህጀር በመነሳት ዛሬ ወደ ሁመራ ኢትዮጵያ መግባታቸው ይታወሳል፡፡
ጎንደር ከተማ ሲደርሱም አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡