የአፍሪካ ህብረትና የሻንጋይ የትብብር ድርጅት ሽብርተኝነትን በጋራ ለመዋጋት ተስማሙ
የአፍሪካ ህብረትና የሻንጋይ የትብብር ድርጅት ሽብርተኝነትን በጋራ ለመዋጋት ተስማሙ
አርትስ 04/04/2011
የአፍሪካ ህብረትና የሻንጋይ የትብብር ድርጅት የፀረ–ሽብር ክንፎች ሽብርተኝነትን መዋጋት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
ሁለት ዓመት ከፈጀ ድርድር በኋላ የተፈረመው ይህ ስምምነት ሁለቱ አካላት በዘርፉ ያላቸውን ልምድ በመጋራት በትብብር ለመስራት ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡
ይህም ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር የሽብር ስጋቶችን በተሻለ ብቃት ለመመለስ እንደሚያስችል ተመልክቷል፡፡
በአውሮፓውያኑ 2001 የተቋቋመው የሻንጋይ የትብብር ድርጅት ሩሲያን ጨምሮ በ8 የኢሲያ እና የአውሮፓ አገራት የተመሰረተ ነው፡፡
ሺንዋ እንደዘገበው የአፍሪካ ህብረት የፀረ–ሽብር ክንፍ ደግሞ አባል አገራትን በማስተባበር ዓለም አቀፉን የፀረ–ሽብር ትግል ለመደገፍ በ2004 በአልጀርስ የተመሰረተ ተቋም ነው፡፡