loading
የአፍጋኒስታን የምርጫ ኮሚሽን ሰራተኞች ላይ የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት ተፈጸመ

አርትስ 19/02/2011

 

ዛሬ በአፍጋኒስታን ካቡል ከተማ አንድ አጥፍቶ ጠፊ በፈጸመው ጥቃት 4 የምርጫ ኮሚሽኑ ሰራተኞች እና ሁለት የጸጥታ ሃይሎች በድምሩ 6 ሰዎችላይ ጉዳት ደርሷል።

የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃቱ የተፈጸመውም ባሳለፍነው ሳምት በሃገሪቱ የተካሄደውን የፓርላማ አባል ምርጫ የድምጽ ቆጠራ እየተካሄደ በነበረበትወቅት ነዉ ተብሏል።

የአፍጋኒስታን የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር ቃል አቃባይ ናጂብ ዳኒሽ እንዳረጋገጠዉ ጉዳቱ ዛሬ ጠዋት በካቡል ከተማ የምርጫ ኮሚሽኑ ዋናመስሪያ ቤት አካባቢ የተፈጸመ ሲሆን 4 የምርጫ ኮሚሽኑ ሰራተኞች እና ሁለት ፖሊሶች ከፍንዳታው ጋር በተያያዘ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

አጥፍቶ ጠፊው በምርጫ ኮሚሽኑ ግቢ ጠባቂዎች አካባቢ ከቆመች ተሽከርካሪ ጋር በመላተም ፍንዳታውን ማድረሱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *