loading
የኢሬቻ በአል በሰላም ተጠናቀቀ

አርትስ20/01/2011

የኦዴፓ የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል በሰላም መጠናቁን ገልፀዋል።

 በሚሊዮኖችየሚቆጠሩ ተሳታፊዎች የኦሮሞ ህዝብ ወዳጆች እና ወንድም  ሕዝቦችን በማሳተፍ እጅግ ደማቅ በሆነ ስነ ስርዓት በሰላም ተጠናቋል በማለት ምስጋና እና ደስታቸውን ገልፀዋል።

የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ‹‹ኢሬቻ ለፍቅር እና ለአንድነት ›› በሚል መሪ ሃሳብ በቢሾፍቱ ከተማ ሆራ አርሰዲ ነው የተከበረው።

የኢሬቻ በአል የኦሮሞ ገዳ ስረዓት መገለጫ እና በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ በስፋት የሚከበር ሲሆን ለፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት ስነስርዓት እንደሆነ እና ስርዓቱም በሁለት አይነት መልኩ እንደሚከናወን ይነገራል፡፡

የመጀመሪያው ኢሬቻ ቱሉ የሚባለው ሲሆን ይህም የበጋወቅት ተጠናቆ የክረምት ዝናብ በሚጠበቅበት ወቅት የክረምቱ ዝናብ ፍሬ የሚፈራበት እንዲሆን፣ እንስሳት እና ሰዎች ለድርቅ እንዳይጋለጡ እና ክረምቱ በሰላም እንዲያልፍ የካቲት ወር አጋማሽ አባቶች  ከፍ ባለ ተራራ ጥላ ባጠላበት ስፍራ ላይ በመሆን ስለክረምቱ በሰላም መግባት እና ስለዝናብ በወቅቱ መጣል  የሚማፀኑበት እና ምስጋና የሚያቀርቡበት ነው፡፡

ኢሬቻ መልካ ወይም ዛሬ የተከበረው ስርዓት ደግሞ ክረምቱ ተጠናቆ  መስከረም ወር አጋማሽ ላይ የክረምቱን በሰላም መጠናቀቅ ፍሬ ማፍራት ዘመድ አዝማድ ተሰባስቦ የባህል ልብስ ተለብሶ እርጥብ ሳር እና አደይ አበባ በመያዝ ‹‹ፈጣሪን እንለምናለን በፈጠረውም ነገር ፈጣሪን እናደንቃለን…››  ‹‹ኦ ያ ማሬዎ…ማሬዎ ›› እየተባለ ምስጋና ፣ፀሎት እና የአባቶች ምርቃት የሚካሄድበት ስርአት ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *