የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በ2010 በጀት አመት ከታክስ በፊት ከ946ሚሊየን ብር በላይ ትርፍ አገኘሁ አለ፡፡
በበጀት አመቱ አጠቃላይ የድርጅቱ ገቢ 1.4 ቢሊዮን እንደነበረ ተናግሯል፡፡
ድርጅቱ 32ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ ባካሄደበት ወቅት የድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ነፃነት ለሜሳ የድርጅቱ ትርፍ ከታቀደዉ በ12.9 በመቶ ብልጫ እንዳለዉና ካለፈዉ አመት ጋር ሲነጻጸር በ35.6 በመቶ ብልጫ እንዳለዉ ተናግረዋል፡፡
በጉባዔው መክፈቻ ላይ የተገኙት የመድን ድርጅት ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዳባ ደበሌ ተቋሙ የፋይናንስ እንደመሆኑ ባለፈው ዓመት የመንግስትን ካዝና ለመሙላት ብዙ ስራዎች መሰራታቸውን አስታውሰው፤ በቀጣይ በሚሰሩ ስራዎችም በሃገሪቱ እየታየ ላለው የኢኮኖሚ እድገት የበኩላችንን ሃላፊነት እንወጣለን ብለዋል፡፡
ዛሬም በካሄዱት ጉባኤ የ2010 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ውጤትና የ2011 በጀት ዓመት የስራ ዕቅድ ላይ መክረዋል፡፡