loading
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ 15ኛ የባንክ አጋሩን ዛሬ አሳወቀ

አርትስ 03/01/2011
ምርት ገበያው የአገልግሎት ተደራሽነቱን ለማስፋትና አገልግሎቱን ለማዘመን ለሚሰራቸው ስራዎች አባይ ባንክን አጋሩ አድርጎ ዛሬ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
የምርት ገበያው ዋና ስራ ስፈፃሚ አቶ ወንድማገኝ ነገራ በፊርማ ሥነሥርዓቱ ላይ ተገኝተው እነዳሉት ኢትዮጵያ ከግብርና ውጤቶች የውጪ ንግድ ከምታገኘው የውጭ ምንዛሬ ሃመሳ በመቶ የሚሆነው በምርት ገበያው የግብይት ሥነ ስረዓት ውስጥ በማለፍ የሚገኝ በመሆኑ የመንግስትን የኢኮኖሚ ፖሊሲ አቅጣጫ በመከተል የተለያዩ የአገልግት ማስፋፊያ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
አባይ ባንክ በበኩሉ ቴክኖሎጂ መራሽ የሆኑ ስራዎች መስራቱን እንደሚቀጥል አሳውቆ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ለሚሰራችው ዘመናዊ ስራዎች ከጎኑ እንደሚሆን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ የኋላ ገሰሰ ተናግረዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *