የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛዉ አገር አቀፍ ምርጫን ለማካሄድ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገለፀ::
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2013 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛዉ አገር አቀፍ ምርጫን ለማካሄድ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገለፀ::ቦርዱ አያደረገ ያለዉን ዝግጅት ለጋዜጠኞች አስጎብኝቷል፡፡ምርጫ ቦርዱ ለምርጫ ከሚያስፈልጉት ቁሳቁሶች 90 በመቶ ያህሉንም ገዝቶ ማጠናቀቁን ገልጿል፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባዘጋጀዉ ጉብኝት ለምርጫ የሚያግዙትን የድምጽ አሰጣጥ ቁሳቁስና ምዝጋበ ሂደት ምን እንደሚመስል በኢግዚቢሽን ማዕከልና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ ዉስጥ ባዘጋጃቸዉ መጋዘኖች አሳይቷል፡፡በጉብኝቱ ወቅት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እንዳስታወቁት ቀጣዩ ምርጫ ከዚህ በፊት በተሻለ ሚስጥራዊ እንዲሆን ጥረት ተደርጓል ብለዋል፡፡
ቦርዱ ከዚህ ቀደም በምርጫ ወቅት የምርጫ ሂደት ምን እንደሚመስልና ለ6ተኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ቀድሞ ነበሩ ቅሬታዎችን ለማስቀረት የተደረገዉን ዝግጅት ለጎብኚዎቹ በንጽጽር አሳይቷል፡፡የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ 6ተኛዉ ሀገር አቀፍ ምርጫን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ 50 ሺህ 9 መቶ ምርጫ ጣቢያ ያዘጋጀ ሲሆን ፤ከድምጽ መስጫ ወረቀቶችና ፤አንዳነድ ቁሳቁሶች በሰተቀር አብዣኛዎቹን ዝግጅቶች ማጠናቀቁን ገልጿል