የኢትዮጵያ ክለቦች አሁንም የባህር ማዶ ተጫዋቾችን ማስፈረማቸውን ቀጥለውበታል
የኢትዮጵያ ክለቦች አሁንም የባህር ማዶ ተጫዋቾችን ማስፈረማቸውን ቀጥለውበታል
ዘንድሮ ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪምየር ሊጉ በድጋሜ የተመለሰው ደቡብ ፖሊስ በኢትዮጵያ ልምድ ያላቸውን ናይጄሪያዊያን አጥቂዎች ፊሊፕ ዳውዝ እና ላኪ ሳኒ አስፈርመዋል፡፡
ቡድኑ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁሉንም የጨዋታ መርሀ ግብሮች አከናውኖ በአምስት ነጥቦች 15ኛ ላይ ተቀምጧል፡፡ በአንጋፋ ተጫዋቾች የተሞላውን ደቡብ ፖሊስ ከአጥቂ ችግሩ ለመላቀቅ የሊጉ የልምድ ባለቤቶች ፊሊፕ ዳውዝ እና ላኪ ሳኒን በአንድ ዓመት የውል ስምምነት ወደ ክለቡ መቀላቀሉን አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ነግረውኛል ስትል ሶከር ኢትዮጵያ በድረ ገፃó አስነብባለች ፡፡
ፊሊፕ ዳውዝ ከዚህ ቀደም ከ2003 ጀምሮ በኤሌክትሪክ፤ ደደቢት፤ ንግድ ባንክ እንዲሁም ከኩዌት እና ሳዑዲ አራቢያ ክለቦች መልስ በድጋሚ ወደ በፋሲል ከነማ ተጫውቷል፤ ይሁን እንጂ ከንግድ ባንክ ጋር ከነበረው ቆይታ ይልቅ በሌሎቹ ስኬታማ ነበር ማለት አይቻልም፡፡
በ2006 በወልቂጤ ከተማ የኢትዮጵያ ቆይታውን የጀመረው ላኪ ሳኒ ደግሞ በጅማ አባ ቡና፣ ሲዳማ ቡና ከዚያ ወደ አርባምንጭ ከተማ አምርቶ በመጫወት በመጨረሻ በአዲስ አበባ ከተማ ቆይታ ነበረው።
ደቡብ ፖሊስ ከጋናዊው ተከላካይ አዳሙ መሐመድ በመቀጠል የውጭ ተጫዋቾችን ቁጥር ወደ ሶስት አሳድጓል፡፡
በሌላ ዜና…
ባህር ማዶ እየተጫወቱ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያ ተጫዋቾች አንዱ የሆነው ሽመልስ በቀለ፤ ከግብፁ ፔትሮጀት የአራት ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ሌላኛው የግብፅ ክለብ ምስር ኢል መቃሳ ጋር በይፋ መፈረሙ ተረጋግጧል፡፡
ሽመልስ በፔትሮጀት ቆይታው ቡድኑን እስከ አምበልነት ደረጃ ያገለገለ ሲሆን በአጣብቂኝ ጨዋታዎች ጭምር ወሳኝ ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል፡፡
ተጫዋቹ ባልተገለፀ ዋጋ ከምስር ኢል መቃሳ ጋር የአራት ዓመት ከግማሽ ውል መፈራረሙን ሶከር የዘገበች ሲሆን ክለቡ በሊጉ በ27 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡