loading
የኢትዮ-እንግሊዝ የቢዝነስ መድረክ በለንደን ተካሄደ።

መደረኩ በኢትዮጵያ ያሉ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለእንግሊዝ ባለሃብቶች ለማስተዋወቅና
ተሳትፏቸውን ማስፋት ዓላማ ያደረገ ነው ተብሏል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ የኢኮኖሚ አማካሪ ዶክተር አርከበ እቁባይ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት
ኢትዮጵያ ለኢንቨስተሮች የምታደርገውን ማበረታቻ ገልፀው፤ ሀገሪቱ  ሰፊ ሀገራዊ፣ አካባቢያዊና
አለምዓቀፋዊ መዳረሻ ገበያዎች ተጋሪ በመሆኗ ፤ያሉት ሁሉም የውጭ ኢንቨስትመንቶች ተጠቃሚዎች
ናቸው ብለዋል።
ከ30 በላይ የኢትዮጵያ ኩባንያዎችን ጨምሮ በርካታ የእንግሊዝ ኩባንያዎች የተሳተፉ ሲሆን
በኢትዮጵያ በርካታ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ተሰማርተው የሚገኙ የእንግሊዝ ባለሃብቶች በኢትዮጲያ
ስላለው ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጭ ገለፃ አድርገዋል።
በተጨማሪም መንግስት የተለያዩ የማሻሻያ እርምጃዎች እየወሰደ በመሆኑ ለኢንቨስተሮች የበለጠ
አመቺ ሁኔታ እንደሚፈጠር እና  የእንግሊዝ ባለሃብቶቸ የጨርቃጨርቅ፣ የቆዳ ውጤቶች፣ አግሮ
ፕሮሰሲንግ፣ ማእድንና ኢነርጂን ጨምሮ በተለያዩ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ሰፊ ተሳትፎ እንዲያደርጉ
ዶክተር አርከበ ጥሪ አቅርበዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *