loading
የእስራኤል አቃቤ ህግ ከምርጫ በፊት ኔታንያሁ ላይ ክስ ልመሰርት እችላለሁ አለ

የእስራኤል አቃቤ ህግ ከምርጫ በፊት ኔታንያሁ ላይ ክስ ልመሰርት እችላለሁ አለ

አቃቤ ህግ የሰጠው ፍንጭ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ሚያዚያ 9 ከሚካሄደው ምርጫ በፊት ሊከሰሱ እንደሚችሉ ያመላክታል ተብሏል፡፡

አቃቤ ህግ በመግለጫው  ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ምርጫው ከመካሄዱ በፊት እንዳይከሰሱ የሚያደርግ ህጋዊ ምክንያት የለም ነው ያለው፡፡

አቃቤ ህግ ይህን ያለው የኔታኒያሁ ጠበቃ ከምርጫው በፊት እንደዚህ ዓይነት አደናቃፊ ውሳኔ አይተላለፍም ማለታቸውን ተከትሎ ነው፡፡

ጠቅላይ አቃቤ ህጉ አቪቻይ ማንዴልብሊት ከስ የመመስረት ሂደቱን ለማፋጠን ማስረጃዎችን በተቻለ ፍጥነት በመመርመር ላይ ነን ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሶስት የተለያዩ  የሙስና ወንጀሎች ክስ እንደሚጠብቃቸው የፖሊስ ምርመራ ያሳያል፡፡

እሳቸው ግን አቃቤ ህግ ፍላጎቱን ይፋ ቢያደርግም እኔን ከምርጫ ውድድር የሚያግደኝ ነገር የለም በማለት ተናግረዋል፡፡

 

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *