loading
የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አጓጊነቱ አሁንም ቀጥሏል

የሊጉ የ35ኛ ሳምንት ግጥሚያዎች በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ተካሂደዋል፤ የሊጉን አሸናፊ እና በቀጣዩ ዓመት የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊ ለመለየት የሚደረገው ትግል አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ትናንት የመርሲ ሳይዱ ሊቨርፑል ወደ ዌልስ ምድር አምርቶ ካርዲፍን በጆርጂኒዮ ዊናልደም እና ጄምስ ሚልነር የፍፁ ቅጣት ምት ጎል 2 ለ 0 በመርታት የሊጉ አናት ላይ መልሶ ተቀምጧል፡፡

ተመሳሳይ ሰዓት በለንደን ደርቢ አርሰናል ኤመሬትስ ላይ በክሪስታል ፓላስ የ 3 ለ 2 ሽንፈት ገጥሞታል፡፡ ለፓላስ ቤንቴኬ፣ ዛሃ እና ማክአርቱር ሲያስቆጥሩ ፤ ለአርሰናል ኦዚል እና ኦባምያንግ አስገኝተዋል፡፡
ወደ መርሲ ሳይድ የተጓዘው ማንችስተር ዩናይትድ ጉዲሰን ፓርክ ላይ በኤቨርተን የ4 ለ 0 አስደንጋጭ ሽንፈት ደርሶበታል፡፡ ቀያይ ሰይጣኖቹ ከሙሉ የጨዋታ ብልጫ ጋር ሲሸነፉ ሪቻርሊሰን፣ ሲጉርድሰን፣ ዲኜ እና ዋልኮት የጣፋጮችን ግቦች ከመረብ አገናኝተዋል፡፡
ቅዳሜ ዕለት ደግሞ ባለፈው ሳምንት አጋማሽ በቻምፒዮንስ ሊጉ አይረሴ ጨዋታ ያስመለከቱን ማንችስተር ሲቲ እና ቶተንሃም ኢቲሃድ ላይ ተገናኝተው በፊል ፎደን ብቸኛ ግብ ሲቲ 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ዛሬ ምሽት 4፡00 የሳምንቱ የማሳረጊያ ጨዋታ ሲደረግ ቼልሲ በስታንፎርድ ብሪጅ በርንሊን የሚገጥም ይሆናል፡፡ ቼልሲ የሚያሸንፍ ከሆነ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ማሳደግ ይችላል፡፡
ሊጉን ሊቨርፑል በ88 ነጥቦች ሲመራ፣ ማ.ሲቲ በ86 ሁለተኛ፣ ቶተንሃ በ67 ሶስተኛ፣ አርሰናል በ66 አራተኛ፣ ቼልሲ በተመሳሳይ 66 ነጥብ በግብ ክፍያ አንሶ አምስተኛ ሲገኝ ማ.ዩናይትድ በ64 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *