loading
የኦሮሚያ የከተሞች ስራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ በ2011 በጀት ዓመት ስራ አጥና በግል ስራ ላይ ለተሰማሩ ወጣቶች 3.283 ቢሊዮን ብር ለመስጠት አዘጋጅቻለሁ አለ፡፡

በዚህም 1.1 ሚሊዮን ወጣቶችን በ90 ማህበራት ለማደራጀት ተወስኗል፡፡ ከነዚህ መካከል 64 ሺህ የሚሆኑት ከመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚመረቁ ናቸው፡፡

ለመፍጠር በተዘጋጀው የስራ ዕድል 52205 ሄክታር የከተማና የገጠር መሬት ተዘጋጅቷል፡፡ እንዲሁም 4648 አዳዲስ ሼዶች የሚገነቡ ይሆናል፡፡

የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ በወቅቱ እንዳሳወቁት ወጣቶች የተፈጠረላቸውን የስራ ዕድል ብቻ ሳይሆን በሃገር የኢኮኖሚ እድገት ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ እንደሚችሉ ማሰብ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

የስራ ባህላችንን በመቀየርም የስራ ዕድሎችን መፍጠር እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *