loading
የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ(ኦብኮ) በምዕራብ ኦሮሚያ ኦነግ እያደረሰ ያለውን ጥቃት አወገዘ

አርትስ 18/04/2011
ኦሮሚያን የጦርነት ቀጠና ለማድረግ እየሰሩ ያሉ አካላት እጃቸውን እንዲሰበስቡ የኦሮሞ ብሄራዊ ኮንግረስ በሰጠው መግለጫ ጠይቋል፡፡

ድርጊቱን ለመመፈጸምና ለማስፈጸም የሚሳተፉ አካላት እጃቸውን እንዲሰበስቡም ፓርቲው አስጠንቅቋል፡

የኦብኮ ሊቀመንበር አቶ ቶሎሳ ተስፋዬ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት ባለፉት 4 አመታት የኦሮሞ ቄሮዎች እንዲሁም የተለያዩየሀገሪቱ የህብረተሰብ ክፍሎች ለውጡ እንዲመጣ ትልቅ ዋጋ ከፍለዋል፡፡

ነገር ግን የኦነግ ታጣቂዎች፣ ንብረት መዝረፍና ሰው በነጻነት ወጥቶ እንዳይንቀሳቀስ እያደረጉ መሆናቸው የሚያሳዝን ተግባር ነው ብለዋል፡፡

የተከፈለው ዋጋ ደግሞ መረጋጋትና ሰላምን ለማምጣት እስከሆነ ድረስ ለውጡን አስጠብቆ መቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል የፓርቲውሊቀመንበር፡፡

በለውጡ ሂደትም እስረኞች መፈታታቸው፤ በሽብርኝነት የተፈረጁ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ወደ ሃገር ቤት መግባታቸውን መልካም ሆኖ እያለበዚህ በለውጥ ሰዓት ለሰው ህይወት መጥፋትና ለንብረት ውድመት መንስኤ መሆን ሊቆም እንደሚገባ ተጠይቋል፡፡

ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የምርጫ ቦርድም ጭምር እየተስተካከለ ባለበት ሁኔታ የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር(ኦነግ) ሰላም ማወክ ተቀባይነት እንዳሌለው የኦብኮ ሊቀመንበር አቶ ቶሎሳ ተስፋዬ ገልጸዋል፡፡

በኦነግ እና የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ODP) መካከል የተደረገው ስምምነት ግልጽ ባለመሆኑም ስምምነቱ ግልጽ ሆኖ ሁለቱ አካላትለመፍትሄ እንዲሰሩም ጠይቀዋል፡፡

እኛ ለውጡን እንደግፋለን፤ ለውጡን ለማስቀጠልም ከመንግስትና ከህዝቡ ጋር ሆነን ለውጡን የሚያደናቅፈውን አካል እንታገላለንምብለዋል በመግለጫቸው ::

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *