loading
የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ) በሚቀጥሉት ሶስተ ቀናት ውስጥ ወደ ኢትዮጲያ ገብቶ ስራ ይጀምራል ተባለ::

በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ ወደአዲስ አበባ ልዑካን እንደሚያሰማራ እና ጽሕፈት ቤቱን ከፍቶ ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንደሚጀምር የድርጅቱ መሪ አቶ ዳውድ ኢብሳ ለ ቪ ኦ ኤ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጲያ መንግስትም በአስመራ ከሚገኘው የ ኦነግ ድርጅት ጋር በኢትዮጲያ ይልቁንም በኦሮሚያ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዴት ህዝቡን ባሳተፈ መልኩፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እንዳለባቸው ከስምምነት መድረሳቸው ነው የተነገረው፡፡
አቶ ዳውድ ድርጅታቸው ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለማድረግ ወደ ኢትዮጲያ ሲገባ የኦሮሞ ሕዝብ እራሱን በራሱ የማስተዳደር ስላጣን አለው የሚለውን ህገመንግስታዊ ነፃነት ከሕዝቡ ጋ ተወያይቶ ውሳኔ የመስጠቱን ጉዳይ ከግምት ውስጥ በማስገባት መሆኑንም ገልፀዋል፡
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቃል አቀባይ ዶክተር ነገሬ ሌንጮ በበኩላቸው ስምምነቱ በኢትዮጲያ መንግስት እና በኦነግ መሀከል የነበረውን ግጭት የሚፍታ ሲሆን በሂደት የሚታዩ ጉዳዮችን የሚገመግም ኮሚቴ ከሁለቱም ወገን በቅርቡ ይዋቀራል ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *