loading
የኮንትሮባንድ እቃዎችን በይፋ በወታደራዊ መኪኖች ጭነው መርካቶ ላይ የሚሸጡት የህወሓት ጀነራሎች

አበባ፣ መስከረም 27፣ 2014  የህወሓት የጦር ጀነራሎች ቀረጥ ሳይከፈልበት የገባ ጐማና የመሳሰሉት የኮንትሮባንድ እቃዎችን በይፋ በወታደራዊ መኪኖች ጭነው መርካቶ ላይ ይሸጡ ነበር ተባለ፡፡ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በተለይ ከ30 እና 40 ዓመት በላይ የሃገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ወጪ የሚጠይቁ እንደ ብረት፣ ኘላስቲክ፣ ኬሚካል እና ጐማ የመሳሰሉትን እቃዎች ከውጭ የማስመጣቱ ሥራ ከ90 በመቶ በላይ በሽብር ቡድኑ እና በሰንሰለቱ ውስጥ በተሰማሩ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ነበር ብሏል፡፡ የአሸባሪው ይህ አሻጥር ምርትን ሰውሮ ለማከማቸት፣ ዋጋን ለመወሰን እንዲሁም በጥቅል የንግድ መስመሩን ለመቆጣጠር ያስቻለ የአደገኛው አሻጥር ገጽታ እንደነበር ተገልጿል፡፡

ሚኒስቴሩ እንዳለው እዚህ ላይ አሸባሪው ቡድን በሃገር ውስጥ ባንኮች የሚገኘውን ጥሬ ገንዘብ ከመመዝበር ባለፈ የውጭ ምንዛሬ ክምችትንም በከፍተኛ ሁኔታ ለራሱ ጥቅም ብቻ በማዋል ሃገርና ህዝብ ጠልነቱን ያሳየበት ነው፡፡ አሸባሪው በግብር ሥርዓቱ ውስጥ የራሱን ሰዎች አሰማርቶ በህጋዊ መስመር የሚነግዱ ነጋዴዎችን ከሚገባው በላይ ግብር በመጫን ከገበያ እንዲወጡ በማድረግ የራሱን ድርጅትና ደጋፊዎቹን ግብር ሳይከፍሉ የሃገርን ኢኮኖሚ እየጐዱ በነጻነት እንዲኖሩ አስችሏል ተብሏል፡፡ የአሸባሪው አሻጥር በጉምሩክ ስርዓቱ ላይም ከፍተኛ ብልሽት የፈጠረ ነበር፡፡

በሁሉም የሃገሪቱ ኬላዎች ማለት በሚቻልበት ደረጃ ከጦር ሰራዊት የተመለሱ የህወሓት አባላትን ብቻ በመመደብ እና ኬላዎችን እንዲቆጣጠሩ በማድረግ ከአሸባሪ ቡድኑ ህገ ወጥ ንግድ እና አሻጥር ጋር በጋራ የሚሰሩ አካላት ቀረጥ ሳይከፍሉ እቃዎችን ከውጭ እንዲያስገቡ ወደ ውጭም እንዲያስወጡ በመፍቀድ
በህጋዊ የንግድ ሰንሰለቱ የሚሰሩ ዜጐች ከውድድር ውጭ እንዲሆኑና እንዲከስሩ ያደርጉ እንደነበር ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *