የዓረብ ሊግ 40 ሀገራት ኢምባሲያቸውን ወደ ኢየሩሌም እንዳያዛውሩ አስቁሜያለሁ አለ፡፡
የዓረብ ሊግ 40 ሀገራት ኢምባሲያቸውን ወደ ኢየሩሌም እንዳያዛውሩ አስቁሜያለሁ አለ፡፡
ይህን ያሉት የህብረቱ ምክትል ዋና ፀሀፊ ሁሳም ዛኪ ናቸው፡፡ ዛኪ እንደሚሉት ይህ ውጤት የተገኘው የዓረብ ሀገራት ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ባደረጉት የጋራ ጥረት ነው፡፡
ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ፍልስጤም ከእስራኤል እና አጋሮቿ የሚደርስባትን ጫና ለመቋቋም በምታደርገው ትግል የዓረብ ሊግ ከጎኗ ይቆማል ብለዋል ዛኪ፡፡
የአውሮፓ ህብረት፣ ቻይና እና መላው ዓለም የተቃወመው የአሜሪካ ውሳኔ ተቀባይነት የለሌው ነው ያሉት ምክትል ዋና ፀሀፊው ዋሽንግተን ራሷን የዓለም ፖሊስ አድርጋ መቁጠሯ ስህተት መሆኑን ማወቅ አለባት ሲሉም አክለዋል፡፡
እንደ ዛኪ ገለፃ ፕሬዝሬዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ የጎላን ተራራዎች የእስራኤል የሉዓላዊ አስተዳደር አካል ናቸው ማለታቸው በስህተት ላይ ስህተት መጨመር ነው፡፡
የዓረብ ሀገራት የፖለቲካ ቁርጠኝነት ኖሯቸው በጋራ መስራት ከቻሉ ከአቅማቸው በላይ የሚሆን ነገር ሊኖር እንደማይችልም ተናግረዋል ዛኪ፡፡
በየመን ያለውን ሁኔታ አስመልክተው ሲናገሩም የዓረብሊግ ዓለም አቀፍ እውቅና የተሰጠውን መንግስት እንደሚደግፍ አብራርተዋል፡፡
መንገሻ ዓለሙ