loading
የገቢዎች ሚኒስቴር ሀገራዊ የታክስ ንቅናቄ መርሃ ግብር ሊካሄድ ነው አለ

አርትስ 10/04/2011

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ግዴታዬን እወጣለሁ መብቴን እጠይቃለሁ በሚል መሪ ቃል መርሃ ግብሩ እንደሚካሄድ አስታውቋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የሚሰበሰበው ገቢ ከሀገራዊ አጠቃላይ ምርት ጋር ያለው ድርሻ 10.7 በመቶ መሆኑን የተናገሩት የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፤ የታክስ አሰባሰብ ስርዓቱ ላይ የሚታዩ ችግሮቸን በጋራ በመቅረፍ ሀገራዊ ለውጡን እንዲደግፍ ማስቻል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ለታክስ አሰባሰብ ስርዓቱ መዳከም የውጭ ንግድ መቀዛቀዝ፣ የተደራጀ ሌብነት፣የታክስ ስወራ፣ኮንትሮባንድ ፣ የደረሰኝ ማጭበርበር እና ግብር የመክፈል ባህል አለማደግ ዋነኛ ምክኒያቶች መሆናቸውን ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

አመቱን ሙሉ በሚካሄደው መርሃግብር ያለባቸውን ግብር በወቅቱና በትክክለኛው መንገድ የሚከፍሉ ግብር ከፋዮች ሽልማት እና እውቅና ይሰጣል ተብሏል።

በፍቃደኝነት ግብሩን የሚከፍልና ግብር መክፈል ባህሉ የሆነ ማህበረሰብ ለመፍጠር የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የገቢ አሰባሰብ ማሻሻያዎች   እንደሚካሄዱም ሰምተናል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *