loading
የጊኒ ተቃዋሚዎች መንግስት በአባሎቻቸው ላይ የወሰደውን እርምጃ አወገዙ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2013 የጊኒ ተቃዋሚዎች መንግስት በአባሎቻቸው ላይ የወሰደውን እርምጃ አወገዙ:: ጊኒ ከአምስት ቀናት በኋላ በምታካሂደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ ለሶስተኛ ጊዜ እወዳዳራለሁ በማለታቸው ምክንያት ከባድ ተቃውሞ ከተቀሰቀሰ ሰነባብቷል፡፡
በሀገሪቱ የሚነቀሳቀሱት ተቃዋሚዎች እንደሚሉት መንግስት የተነሳበትን ተቃውሞ ለማስቆም በወሰደው የሃይል እርምጃ ከ90 በላይ ሰዎች ተገድለዋል፡፡

የጊኒ የደህንነት ሚኒስትር አልበርት ዳማንታንግ ካማራ ግን በተቃዋሚዎቹ በኩል የቀረበውን የሟቾች ቁጥር ፖለቲካዊ ትርፍ ለማግኘት ካልሆ ሀሰት ነው በማለት አጣጥለውታል፡፡ ይሁን እንጂ ለተቃውሞ አደባባይ በወጡ ነዋሪዎችናበፀጥታ ሰዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይዎት ማለፉን አንክድም፣ በሁኔታውም አዝነናል ብለዋል፡፡

የጊን ህገ መንገስት አንድ ፕሬዚዳንት ከሁለት ጊዜ በላይ መወዳደር አይችልም ቢልም የ 82 ዓመቱ ኮንዴ ግን ለሶስተኛ ጊዜ በዕጩነት ቀርበዋል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ ራሳቸውን ለምርጫው ለማመቻቸት ሲሉ ባለፈው ዓመት የህገ መንግስ ማሻሻያ ካደረጉ ጀምሮ ሀገሪቱ በርካታ ህዝባዊ ተቃውሞዎችን አስተናግዳለች፡፡ አመንስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም በበኩሉ ከ13 ቀናት በፊት 50 ጊኒያዊያን በፀጥታ ሰዎች መገደላቸውን ገልፆ መንግስት በድርጊቱ ፈፃሚዎች ላይ መንግስት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አቅርቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *