የጋሞ ወጣቶች ኢሬቻ በዓል ላይ ለመሳተፍ ወደ ቢሾፍቱ ሊጓዙ ነው
አርትስ 18/01/2011
ከቀናት በፊት መነሻቸውን ቡራዩ ከተማ አድርገው የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች ወደ ጋሞ ሄደው የመስቀል በዓልን ማክበራቸው የታወሳል፡፡
በዓሉን በደቡብ ክልል እያከበሩ በነበሩበት ወቅት የኦሮሚያ ክልል መንግስት ባደረገላቸው ጥሪ መሰረት 30 ሚሆኑ የጋሞ ወጣቶችና የሃገር ሽማግሌዎች በቢሾፍቱ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓል ለማክበር ጥሪ ተቀብለው ነገ ወደ ቢሾፍቱ የጓዛሉ፡፡
የኦሮሚያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ሚልኬሳ ሚደጋ ለአርትስ እንደተናገሩት ክልሉም ሆነ የበዓሉ አዘጋጆች እንግዶችን በታላቅ አክብሮት ለመቀበል ዝግጅት ተጠናቋል፡፡
ጋሞ በነበራቸው ቆይታ ደስተኞች እንደነበሩ የነገሩን ዶ/ር ሚልኬሳ ሁነቱ ሃገራዊ አንድነትንና መተሳሰብ በመሃላችን እንዲኖር ከፍተኛ አስተዋፅዖ አለው ብለዋል፡፡
በቀጣይም ሌሎች ሰፊ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ሊኖር እንደሚገባ የአሁኑ ግንኙነት ማሳያ ነዉ ብለዋል፡