loading
የግብፅ ፓርላማ በዛሬው እለት የአልሲሲን ስልጣን ለማራዘም ድምፅ ይሰጣል፡፡

የግብፅ ፓርላማ በዛሬው እለት የአልሲሲን ስልጣን ለማራዘም ድምፅ ይሰጣል፡፡

ፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር እስ 2034 በስልጣን እንዲቆዩ ያቀረቡት የህገ መንግስት ማሻሻያ ሀሳብ ዛሬ በምክር ቤቱ አባላት ምርጫ ይደረግበታል፡፡

ህገ መንግስቱ እንዲሻሻል ሙሉ ድጋፍ ካገኘ በሁለቱም ምክር ቤቶች ፀድቆ ወደ ስራ ከመግባቱ አስቀድሞ ለህዝበ ውሳኔ ይቀርባል ተብሏል፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው የህጉ መፅደቅ አልሲሲን ተጨማሪ ሁለት የስልጣን ዘመናትን እንዲወዳደሩ ከመፍቀዱም ባሻገር በአንድ የስልጣን ጊዜ የነበረው የ4 ዓመት ጊዜ ወደ 6 ዓመት ከፍ እንዲልም መብት ይሰጣል፡፡

ህገ መንግስቱ ፕሬዝዳንቱ ዳኞችን እና አቃቤ ህጎችን የመሾም ስልጣን የሚሰጥ ሲሆን የመከላከያ ሀይሉም በፖለቲካው ውስጥ ተፅእኖ አንዲኖረው በር ይከፍታል ተብሏል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *