የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የ˝ፀረ ጥላቻ ንግግር˝ን አዋጅ አያረቀቀ ነዉ፡፡
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የ˝ፀረ ጥላቻ ንግግር˝ን አዋጅ አያረቀቀ ነዉ፡፡
ጠቅላይ አቃቤ ህግ ከ˝ፀረ ጥላቻ ንግግር˝ አዋጅ በተጨማሪ በርካታ ህጎችን በማሻሻል ላይ እንደሚገኝ ሰምተናል፡፡
በጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዝናቡ ቱና ለአርትስ እንደተናገሩት የ˝ፀረ ጥላቻ ንግግር˝ አዋጅን የሰዎችን የመናገር ነፃነት ሊገድብ በማይችል መልኩ እና ከህግ መንግስቱ ጋር ሊጋጭ በማይችል መልኩ ለማፅደቅ አስፈላጊ ጥናቶች ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
ከሌሎች ህጎች ፈጥኖ የሚጸድቀው ይህ ˝የፀረ ጥላቻ ንግግር˝ አዋጅ ኢትዮጵያ ላይ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ብሄሮች እና ማንነቶች ላይ በጥላቻ ንግግር ምክንያት የሚደርሰውን ችግር እና ግጭት ለማስቀረት እንደሚያግዝ አቶ ዝናቡ ተናግረዋል፡፡