loading
ደቡብ ፖሊስ እና ሙሉዓለም ረጋሳ ተለያይተዋል

ደቡብ ፖሊስ እና ሙሉዓለም ረጋሳ ተለያይተዋል

 

በ2010 ዓ/ም የውድድር ዓመት ወደ እግር ተመልሶ መጫወት የጀመረውና በዓመቱ መጀመርያ ደቡብ ፖሊስን ተቀላቅሎ የነበረው አንጋፋው አማካይ ሙሉዓለም ረጋሳ ከክለቡ ጋር ተለያይቷል።

ለሁለት ዓመታት ከሜዳ ከራቀ በኋላ 2010 በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ አማካኝነት ከወራት በላይ የፈጀ የሙከራ ጊዜን አሳልፎ ለሀዋሳ ከተማ በመፈረም በድጋሚ እግር ኳስን መጫወት የጀመረው ሙሉዓለም መልካም የውድድር ዓመት በማሳለፍ በክረምቱ ለሌላኛው የሀዋሳ ክለብ ደቡብ ፖሊስ በአንድ አመት የውል ስምምነት ተቀላቅሎ ነበር፡፡

በመጀመሪያው ሊጉ የውድድር ዘመን ለክለቡ ወጣ ገባ እያለ ሲጫወት የቆየ ቢሆንም በሁለተኛው ዙር ከክለቡ ጋር እንደማንመለከተው ታውቋል።

ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም በቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ሰበታ ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ከሚጠቀሱ ድንቅ አማካዮች አንዱ ነው፡፡

ደቡብ ፖሊስ ከሙሉዓለም ቀደም ብሎ ከግብ ጠባቂው ዳዊት አሰፋ እና ቴዎድሮስ ሁሴን ጋር መለያየቱ የሚታወስ ሲሆን ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችንም ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።

የመረጃው ምንጭ፡- ሶከር ኢትዮጵያ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *